Thursday, April 14, 2016

ክክክክ የሚገርም ጉድ


በዚህ ክፍል ደግሞ በመድረክ ላይ ሆኖ ከተናገራቸው ቃላት ወስጥ የተወሰኑትን እንይ
1•"ልጸልይላችሁ" ይህንን ቃል ስሰማ በጣም ገረመኝ ምክንያቱም ትናንት ከትናንት ወዲያ በየቦታው አማላጅ አያስፈልግም፣ ድንግል ማርያም አታማልድም፣ ቅዱሳን አያማልዱም እያሉ ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ዛሬ እንዲህ አይነት ቃላትን ሲቀበሉ ስላየሁ ነው። እዚህ ላይ ማየት እና ማስተዋል ያለብን ነገር
* በእውኑ ይህ ሰው ከቅድስት ድንግል ማርያም ይበልጣልን? የሚለውን ጥያቄ ነው። ይህ ሰው እንኳን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሊበልጥ እና እኩል ሊሆን እግሯ የረገጠውን ትቢያ እንኳ መሆን አይችልም። ድንግል ማርያም ማለት አደፍ ጉድፍ የሌለባት ንጽሕት ዘር ናት። ነቢያት ትንቢት የተናገሩላት፣ ምሳሌ የመሰሉላት፣ አዳም ከወደቀበት የኃጢአት ጉድጓድ የወጣባት፣ ሔዋን ከታሰረችበት የኃጢአት ማሰሪያ የተፈታችባት፣ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር የነበረች በኋላም የተስፋው ጊዜ ሲደርስ አምላክን በማህጸኗ ለመሸከም በቅታ የተገኘች በአጠቃላይ ለፍጥረታት ሁሉ የድህነት ምክናያት የሆነች ድንቅ ልዩ ፍጥረት ናት። ስለዚህ አባቶቻችን ስለ ድንግል ማርያም የተነገረውን እና የተደረገውን ነገር ሁሉ ጠንቅቀን መናገር አይቻለንም እና ዝም እንበል እንዳሉ ሁሉ እኛም ከእነሱ አንበልጥም እና አፈጣጠሯን እና ልዩ ጸጋዋን እያደነቅን በበረከቷ በአማላጅነቷ በእናትነቷ ጸጋ መጠቀም ይሻለናል። ስለዚህ ድንግል ማርያምን አታማልድም ብሎ በድፍረት የተሳደበ አፍ ዛሬ እኔ አማልዳለሁ(ለሌሎች እጸልያለሁ) ሲል መስማት በጣም የሚገርም ነገር ነው። የሚናገረው ሰውም ጤነኛ አዕምሮ የለውም። የሱን ሀሳብም በእልልታ እና አሜን በማለት የተቀበሉ ሰዎች በእውነት መነሻ እና መድረሻቸውን ያላወቁ፣ ሁለት የማይጣጣም ነገርን በአንድ ይዘው ለመጓዝ የሚሞክሩ፣ ለጊዜው በስጋዊ ፈቃዳቸው ደስተኛ ሆነው ማለትም አንዴ ጸድቀናል በሚል ተልካሻ ምክናያት እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ኃጢአትን ለመስራት የሚፈልጉ ሞኞች ናቸው። እዚህ ላይ ሌላው ማስተዋል ያለብን ነገር ቅዱሳን ቅድስናቸውን ያገኙት ስለአምላካቸው በአላውያን ነገስታት እና በሀሳውያን ነቢያት ፊት መስክረው የደረሰባቸውን መከራ እስከ ሞት ድረስ በመታገስ እና በጸኑ መከራ ወስጥ በማለፍ ነው። ቅድስናቸውንም የመሰከረላቸው መከራውን እንዲታገሱ ጽናት እና ትዕግስት እንዲሁም ማስተዋልን የሰጣቸው ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካቸው ነው። ስለዚህ መናፍቃን የቅዱሳንን ቅድስና ተቀበሉም አልተቀበሉም ለራሳቸው ይቀርባቸዋል እንጅ ከቅዱሳን የሚቀንሱባቸው አንዳች ነገር የለም። ምክናያቱም እግዚአብሔር ያከበረውን ማንም ዝቅ ማድረግ አይችልም እና ነው። በአጠቃላይ እንዲህ አይነት ነገሮችን) የምናመዛዝንበት ህሊና ስለተሰጠን መጥፎውን ከጥሩው፣ ጨለማውን ከብርሐን ለይተን እራሳችንን አውቀን ጥሩውን መንገድ ልንከተል ያስፈልጋል። ድንግል ማርያም በምልጃዋ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ትሰውረን አሜን

No comments:

Post a Comment