እሱም ከፍተኛ ሞራል ስለተሰማው እራሱን ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር
በማስተካከል ልሳን ተገለጸልኝ በሚል መንፈስ እንኳን ለሚሰሙት ለራሱ እንኳ ትርጉሙን በማያውቀው ቋንቋ በመሰለ ነገር
ይንተባተብ ጀመር። ልብ ብሎ በእውነተኛ ህሊና ለሚመለከተው እና ለሚመረምረው ሁሉ ነገሩ ርኩስ መንፈስ በሰዎች ላይ
ሲሰለጥን የሚመጣ ባዶ መንተባተብ እንጅ የመንፈስ ቅዱስ አይደለም። ምክንያቱም ከቅዱሳን ሐዋርያት እና ከቀደሙት
ቅዱሳን አባቶቻችን እንደሰማነው እና እንደምንረዳው በመንፈስ የተገለጠላቸው ልሳን ተናጋሪዎችም ጠንቅቀው የሚያውቁት
ትምህርታቸውን የሚከታተሉት ሰዎችም ራሳቸው በሚያውቁት እና በሚግባቡበት ቋንቋ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል።
የሐዋርያት ስራ 2:6—12 ስለዚህ በዚህ ሰውየ ላይ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታል ብለው የሚያምኑ ሰዎች
በእውነት መጽሐፍ ቅዱስን ተሸክመው የሚዞሩ እና ከላይ ከላይ ለእነሱ ብቻ የሚመቹ ጥቅሶችን የሚያነበንቡ ምስጢሩ
ግን ያልገባቸው ለሰው ልጆች ሁሉ ብርሐን የሆነችውን አንዲቱን ተዋህዶ እምነትን እንዳይከተሉ ዘመናዊ በሆነ ጠንቋይ
ቅሰጣ አይነ ልቡናቸው የታወሩ ሰዎች መሆናቸውን ሳይ በጣም ተገረምኩም አዘንኩም። ስለዚህም ነገር ሌሎችም የውሃን
የሆኑ ሰዎች የሚያዩት እና የሚሰሙት ነገር እውነት መስሏቸው እውነተኛዋን መንገድ ትተው ወደ ጨለማ እንዳይገቡ
ለማሳሰብ ስል ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ተገደድኩ። አምላከ ቅዱሳን ከገቡበት የጨለማ ሕይዎት ወደ ብርሀን ይመልሳቸው
እኛንም ከእንደዚህ አይነት መጥፎ ሕይዎት ይጠብቀን አሜን!!! ሌላ ብዙ የገረመኝ ነገር ስላለ በክፍል ሦስት ጠብቁኝ
ይቀጥላል

No comments:
Post a Comment