ይህንን ቃል የተናገረው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ አንድ አንድ ጊዜ ይህንን ቃል በምናነብበት እና በምንሰማበት ጊዜ እንዴት ዐይን እያላቸው ማየት አይችሉም? የሚል ጥያቄ በውስጣችን ሊነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ገባ ብለን ወስጡን ስንመለከተው “ዐይን እያላቸው ማየት የማይችሉ” ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ በወቅቱ የነበረው ነቢይ ለጊዜው የተናገረው በተለያየ መልኩ ተሰርተው በሰዎች ዘንድ ይመለኩ የነበሩ ጣዖታትን ለመግለጽ ፈልጎ ነው፡፡ ቃሉ ግን በተለያየ ጊዜ የተነሱ ሰዎችን ማለትም ሁሉን መርምሮ ማወቅ የሚችል ኅሊና ተሰጥቷቸው ብርሃኑን ከጨለማ፣ እውነቱን ከሃሰት፣ ጥሩውን ከመጥፎው ለይተው እራሳቸውን አና የሚከተላቸውን ሰው በመጥቀም ፈንታ ሰውን የሚጎዱ እና በተሳሳተ መንገድ የሚመሩ ብዙ ሰዎችን ይገልጻል፡፡እንደዚህ አይነት ሰዎች በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በተለያዩ ዘመናት ተነስተዋል አሁንም አሉ ወደፊትም ይቀጥላሉ፡፡ከነዚህም ውስጥ በዘመነ ነቢያት የነበሩት እግዚአብሔር በነቢያቱ አድሮ የሚያስተላልፈውን ትምህርት አና ተግሳጽ ወደ ጎን በመተው እና በራሳቸው መንገድ በመሄድ ፍጻሜያቸው ስቃይ እና ሞት የሆነባቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ከዚህ ዘመን በኋላ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም በመጣበት ጊዜ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚያሰተምረውን ትምህርት እየሰሙ፣ የእጁን ታምራት እያዩ በአጠቃላይ የሚያደርገውን ድንቅ የሆነ ነገር እያዩ እንዳላዩ ሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሁልጊዜ ይቃወሙት ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይቃወሙት የነበረ ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን እነሱ የነበራቸውን ስጋዊ አላማ፣ወስጣዊ ፍላጎት፣ ዝርፊያ እንዲሁም እራሳቸውን ጻድቅ፣ እውነተኛ እና ለስራዓቱ ተቆርቋሪ በመምሰል በውስጣቸው ግን መራራ፣ ድብቅ የሆነና ከእውነት የራቀ ህዝቡን የማደናገር ሴራ ስለነበራቸው ይህንን ጉዳያቸውን ያደነቅፍብናል ብለው ስለሚያስቡ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ውስጡ ጥበበ እግዚአብሔር ቢኖርበትም ጌታችንን ለመስቀል በቅተዋል፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ያሰቡት ነገር ሳይሳካላቸው መቅረቱ ነው፡፡ ምክናያቱም ከእርሱ የተማሩት ሐዋርያት በአምላካቸው መሪነት ጨው በመሆን ከጽንፍ እሰከ ጽንፍ ወንጌልን በማስተማር አልጫ የነበረውን ዓለም አጣፍጠዋል፡፡ ዐይን እያላቸው የማያዩ ሰዎች በሰማዕታት ዘመንም ተነስተው ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችንን በልዩ ልዩ ስጋዊ መከራ በማሰቃየት ለሰማዕትነት አብቀተዋቸዋል፡፡ ሰማዕታትም የሚመጣባቸውን መከራ በመታገስ እና ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላካቸውን ስም በመጥራት እና እስከሞት ድረስ በመታመን የድል አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡ ከሐዋርያት የተረከቧትን እወነተኛዋን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትንም ከእነሱ በኋላ ላለው ትውልድ አስተላልፈዋል፡፡ከእነሱ በኋላ የተነሱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንም ሳትበረዝ እና ሳትከለስ አሁን ላለው ትውልድ አስተላልፈዋታል፡፡ የሚገርመው ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የተነሱ ሆድ አደሮች፤ አይነ ስጋቸው ብቻ የተከፈተላቸው አይነ ልቡናቸው ግን የታወረባቸው፤ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ከገለጻቸው ጣዖታት የማይሻሉ ማለትም ሕይዎት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ጣዖታት የሚያሰሙት የትታደስ ጩኸት ነው፡፡ በጣም የሚገርም እና የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ በእውኑ እነዚህ ሰዎች የእምነት አርበኛ ከነበሩት፣ ሌሊት ከቀን ለጸሎት እና ለስግደት ይተጉ ከነበሩት፣ ሀይማኖታችንን አናስለውጥም፣አንክድም ብለው እሰከመጨረሻው ድረስ በመታገስ መራራ ሞትን ከቀመሱት ቅዱሳን አባቶቻችን ይበልጣሉን? ይህንን ጥያቄ ሁላችን በህሊናችን ልንጠይቅ ያስፈልጋል፡፡ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ሆይ እነዚህ ሰዎች እራሳቸው ጠፍተው ሰውን ለማጥፋት የተነሱ የዲያብሎስ መልእክተኞች ናቸውና ማንነታቸውን በመረዳት ከቤታችን ልናስወጣቸው ያስፈልጋል፡፡ በምን እናውቃቸዋለን ብንል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መመሪያ ሰጥቶናል ይኸውም “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” የሚል ነው፡፡ ማንም ሰው ጌታችን በደሙ ከመሰረታት እና ለሐዋርያት ከሰጣት ከአንዲት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና ስርዓት ውጭ እንግዳ ትምህርት እና የእምነት ዶግማ እንዲሁም ቀኖና እና ስርዓት የሚያመጣ ሁሉ እርሱ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወገን አይደለም፡፡እነዚህ ሰዎች ምንም ሳይማሩ ታሪክ አዋቂ በመምሰል እና አዲሱን ትውልድ ለማወናበድ እንዲሁም በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የአባይ ጉዳይ እንደ ክፍተት በመጠቀም አሁን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያለውን አውነተኛ ዶግማ እና ስርዓት የግብጽ ሰዎች ኢትዮጵያን ለመበቀል እና ኋላቀር ለማድረግ ያመጡት ስርዓት ነው በማለት የትታደስ ጩኸት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ግን እነሱ እንደሚሉት አይደለም፡፡ ስለዚህ ክፍተት የሚመስሉ ነገሮችን እንደ መነሻ ሀሳብ በማንሳት እውነታውን ግን ጥላሸት በመቀባት በአባቶቻችን ዘመን ታይቶ የማይታወቅ አስተምህሮ ቀስ በቀስ ወደቤተክርስቲያን ውስጥ በማስገባት፤ እያወቁም ይሁን ሣያውቁ የሚከተሏቸውን የውኃንን ለዲያብሎስ እራት ለማድረግ የሚተጉ፣ ዐይን እያላቸው የማያዩ እና የማያስተውሉ ተሃድሶወችን ይህንን ስውር ሴራ እንደያዙ አውቀን ልንቃወማቸው ያስፈልጋል፡፡ አምላክ ቅዱሳን ቤተክርስትያናችንን ከውጭ ወራሪ ከውስጥ ጠላት ይጠብቅልን እኛንም በቤቱ ያጽናን አሜን!!!
Thursday, April 14, 2016
“ዐይን ቦሙ ወኢይሬእዩ” “ዐይን አላቸው አያዩም” መዝ 113፡13

Subscribe to:
Post Comments (Atom)

No comments:
Post a Comment